
የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የውይይት መድረክ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት PHEM ዳይሪክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በድሉ ባዴጎ የኤች አይ ቪ ሥርጭትን ለመግታት እየተሰሩ ያሉ የቅኝት ሥራዎች አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በተለይ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰብ አባላት ላይ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶ በመሠራቱ አበረታች ዉጤት መመዝገቡን አሳስበዋል።
በመቀጠልም የዓመቱ የኤች አይ ቪ ሰርቪላንስ ሪፖርት ዶ/ር አፌንሻ አመሎ ካቀረቡ በኋላ ጠንካራ ውይይት በማድረግ ጥንካሬና ክፍተት በመለየት ቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ለመደገፍ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት
ነሐሴ 12/2017ዓ.ም
ሀዋሳ፣ ሲዳማ
ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et


























