Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 ዓ.ም የጥናትና ምርምር ፕሮፖዛሎች (Research proposals presentation) ቀርበው ውይይት ተካሄደ።

በዛሬው ዕለት ማለትም በጥቅምት 12፣ 2018 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የጤና ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀው ወርሃዊ የጥናትና ምርምር ፕሮፖዛሎች የማቅረብ መድረክ ተካህዷል፡፡ ይህም ወርክሾፕ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡበትና ሙያዊ ውይይት የሚያደርጉበት መድረክ ሲሆን፣ ተመራማሪዎች በክልሉ በተለዩና ቅድሚያ በተሰጣቸው ጥናቶችን በማቅረብ የሚማማሩበት መድረክ ነው ፡፡

በዕለቱም የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመኔ ዳባልቄ የወርክሾፑ ዓላማ ተመራማሪዎች የጥናት ውጤቶቻቸውን በማቅረብ ውይይት እንዲደረግ የሚያስችል፣ መማማሪያና አቅም መገንቢያ መድረክ በመሆኑ አገልግሎቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በኢንስቲትዩቱ በተለዩና ቅድሚያ በተሰጣቸው የእናቶችና የህጻናት ጤና፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ የሚያተኩሩ የጥናት ፕሮፖዛሎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም ለተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ሃላፊዎች፣ አስተዳደር አባላት፣ ከፍተኛ ተመራማሪዎች፣ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ሙያዊ ኤክስፐርቶች እና ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የሲዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት

ጥቅምት 13/2018ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን

“”””””””””””””””””””””””””””

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *