Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ መንግስት ለሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ማዕከል የአምቡላንስ መኪና እና 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

ሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ማዕከል የኩላሊት እጥበት ህክምና መስጫ ማዕከል አስመረቀ።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ናቸው የኩላሊት እጥበት ማዕከሉን መርቀው በይፋ ስራ ያስጀመሩት።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የማዕከሉን ባለራዕይ እና መስራች ያላቸውን የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ አድናቆት ገልፀው፤ ይህ ማዕከል ቀጣይነት እንዲኖረውና የሀገርና የትውልድ ባለውለታ የሆኑ አባቶቻችን እና እናቶቻችን በዕድሚያቸው የሚገባቸውን እንክብካቤና ህክምና እንዲያገኙ በተለያየ መልኩ አስተዋጿቸውን እያበረከቱ ያሉ ቅን ልቦችን አመስግነዋል።

ሜሪጆይ ኢትዮጵያዊ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በርካታ አረጋዊያንን ከጎዳና በማንሳትና ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በሀላፊነት እና በቁርጠኝነት በመወጣት ረገድ አርዓያነቱን በተግባር ያረጋገጠ ተቋም መሆኑን የገለፁት ርዕሰ-መስተዳድሩ፤ እንደሀገር በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን የኩላሊት እጥበት ማዕከል በራሱ ጊቢ ማስገንባቱ እና አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የማዕከሉን አቅም የሚያጎለብት ከመሆኑም ባሻገር፤ ተጠቃሚዎቹን ከአላስፈላጊ እንግልትና ስቃይ የሚታደግ መሆኑን ነው ያስረዱት።

ማዕከሉ የተጠናከረ እንዲሆን የክልሉ መንግስት ቀደም ሲል ሲያደርግ እንደነበረው ድጋፉን የሚቀጥል መሆኑንም ርዕሰ-መስተዳድሩ ገልፀዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው እንደሀገር ለአቅመ-ደካሞች በሚደረገው ድጋፍና ክብካቤ ከመንግስት ባሻገር እንደ ሜሪጆይ ያሉ በጎ አድራጎት ተቋማት ትልቅ አበርክቶ እንዳላቸው ነው የገለፁት። እንደዚህ ያሉ ተቋማት ለተገልጋዮቻቸው የህክምና አቅርቦት እንዲኖራቸው ማስቻል ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ነገር ለማድረግ ከጎናቸው መሆኑን ነው ገልፀዋል።

በሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ አረጋውያን ማዕከል ውስጥ ለተገነባው የኩላሊት እጥበት ህክምና መስጫ በርካታ ኢትዮጵያዊን ድጋፋቸውን ማድረጋቸው በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በመርሀ -ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:

👇
👇
👇
👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:

https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/@sidamahealthbureau?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:

https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *