Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የጤና ደህንነት አቅም ለማጠናከር የሚያስችል ግምገማ በክልል ደረጃ ተጀመረ

በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ እና የአንድ ጤና ፅ/ቤት፣ ከሲዳማ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ አለም አቀፍ የጤና ድርጅት እና ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር የሲዳማ ክልል የጤና ደህንነት አቅም ለማጠናከር የሚያስችል የግምገማ አውደ ጥናት ከሰኔ 4 እስከ 6 /2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው::
የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ስራዎችን በሚገባ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያገለግሉ 19 ቴክኒካል የሙያ ዘርፍ ላይ ግምገማ በማድረግ የጤና ደህንነትን አቅም በመገንባት ረገድ በአፍሪካ ከናይጄሪያ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ነች።
የግምገማሂደቱበሁሉም ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህየሲዳማ ክልል የጤና ደህንነት ግምገማ የመጀመሪያው ሆኗል::በግምገማዉ የሲዳማ ክልል ከጤና ደህንነትአንፃር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ በክልሉ ያሉ ጠንካራ ጎኖች እንዲሁም የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ እቅድ በማዘጋጀት የአቅም ግንባታ ስራዎችን ተግባራዊ ለማድግ ያለመ ነው::
ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ የሆኑ ችግሮችን አለም አቀፍና ወቅታዊ ሁኔታዎች በሚጠይቁት ደረጃ የመቆጣጠር ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ አቅምን ለማጠናከር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን፤ ለዚህም ለጤና ደህንነት የሚያገለግሉ ቴክኒካል የሙያ ዘርፎችን በመገምገም አቅምን የመገንት ስራ ኢንስቲትዩቱ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ መሆኑንና የሕብረተሰቡን የጤና ደህንነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ዶ/ር ፈይሳ ረጋሳ የዓለም አቀፍ የጤና ደንብና የአንድ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊበበኩላቸው ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ እና ሀገር አቀፍ ወቅታዊ የጤና ሁኔታዎችን አስመልክቶ በፅሑፍ መረጃዎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ የሲዳማ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተርዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ እናየሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ ፕሪንሲፓል ማናጀር የሆኑት ወ/ሮ ምንትዋብ ግደይ የግምገማ መድረኩን አስመልክቶ ንግግር አድርገዋል፡፡
የሲዳማ ክልል የጤና ደህንነት ከቴክኒካል የሞያ ዘርፎች አንፃር ምን ላይ እንዲሚገኝ በመለየት በቀጣይ ዓመታት የሚሰሩ የአቅም ግንባታ እቅዶች ማዘጋጀትበግምገማ መድረኩ የሚከናወን ሲሆን የጤና ሚኒስቴር ፣ የግብርና ሚኒስቴር ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፣ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን፣ እና በሲዳማ ክልል የተለያዩ ተመሳሳይ ባለድርሻ መስሪያ ቤት ኃላፊዎች፣ ተወካዮችና ባለሙያዎች በመድረኩ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *