Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በክልላችን ባሉ ጤና ተቋማት ላይ የሚሰራው የተቀናጀ ውጫዊ ጥራት ቁጥጥር ስርዓት ወደ ዲጂታል መቀየሩ ተገለጸ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የውጫዊ ጥራት ቁጥጥር ማዕከል ከሆኑ ተቋማት ላቦራቶሪ ባለሙያዎች እንዲሁም ከየወረዳ ለተወጣጡ ለቲቢና ወባ ተወካዮች ”የውጫዊ ጥራትና ቁጥጥር መተግበሪያ ዳታቤዝ” በሚል ርዕስ ለአምስት ቀን ስሰጥ የነበረ ስልጠና ተጠናቀቀ።
በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳ/ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በአጠቃላይ ውይይት እንደገለጹት የተቀናጀ ውጫዊ ጥራት ቁጥጥር በወባና በቲቢ ላይ እየተሰራ የቆየ ብሆንም እንደ ሀገር ከእስላይድ መሰብሰብ አንስቶ ሙሉ በሙሉ ወደ በዲጂታል ስርዓት መቀየሩ በየደረጃው የነበሩ ተግዳሮቶችን እንደሚፈታ ታስቦ የተሰራ መሆኑን በመጥቀስ እንደ ክልል ስራውን እውን ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በአጽንኦት እንድተገብሩ አሳስቧል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 3/2017ዓ/ም
ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *