Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠት ጀመረ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግንቦት 6/2017 ዓ.ም
የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆናቸው ህፃናት ለአስር ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ በይፋዊ የክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ተገልጿል።
በማስጀመሪያ መርሀ-ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ በላይነህ በቀለ እንዳሉት በሀገራችን መከላከልን መሰረት ባደረገው የጤና ፖሊሲ ማህበረሰቡን ከአስከፊ ህመምና ሞት መታደግ እንደተቻለ ጠቁመው በቅርቡ የተከለሰው የጤና ፖሊሲም የቤተሰብ ጤናን ይበልጥ የሚያሻሽልና የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎቶችን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።
ሀላፊው አክለውም ህፃናትን ከአስከፊ ህመምና ሞት የምንከላከልበት የክትባት አገልግሎት በመደበኛነት ከሚሰጠው በተጨማሪ ከግንቦት 6/2017 ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ከ900 ሺህ በላይ ህፃናትን ለመከተብ እቅድ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል ።
በመሆኑም ዘመቻው ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም የጋራ ሃላፊነት በመሆኑ አጋር ድርጅቶች ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ዘመቻውን ስኬታማ እንዲያደርጉ አቶ በላይነህ በክልሉ ጤና ቢሮ ስም ጥሪ አስተላልፈዋል ።
ወላጆች/አሳዳጊዎች እንዲሁም ባለድርሻ ሴክተሮች እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ፣ ክትባት ያቋረጡም ሆነ ምንም አይነት ክትባት ያላገኙ ህፃናትን በሙሉ በአቅራቢያቸዉ በሚገኙ የጤና ተቋማትና ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች በመዉሰድ ማስከተብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም በዘመቻዉ ከኩፍኝ ክትባት በተጨማሪ የቫይታሚን ኤ እደላ፣ የስነ ምግብ እጥረት ልየታ፣ የፀረ አንጀት ጥገኛ ትላትል ኪኒን እደላ፣ የኮቪድ-19 ክትባት ፣የፌስቱላና የማህፀን ውልቃት ችግር ያጋጠማቸውን መለየትና ወደ ህክምና መላክ ከክትባቱ ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰጡ ተመላክቷል።
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተካሄደው ይፋዊ የክትባት ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አካላትና ባለሙያዎች፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች፣ አጋር ድርጅቶች፣የሚዲያ አካላትና የሞቲቴ ፉራ ስታፎችና ተገልጋዮች ተገኝተዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:
👇
👇
👇
👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM
https://www.facebook.com/100064935574057/posts/1065870482254128

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:

https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/@sidamahealthbureau?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:

https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *