
በክልሉ ጤና ቢሮ ለበጀት ዓመቱ ከታቀደው ዕቅድ መነሻ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የየዘርፉ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው እንደሚገመገም መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ገልጸዋል።
ዶ/ር ሰላማዊት አክለውም በዚህ መድረክ ከየሥራ ክፍሎቹ ከሚቀርቡ ሪፖርቶች መነሻ በጥንካሬ እና በጉድለት የተለዩ ጉዳዮች ዙሪያ አጽንኦት ተሰጥቶ ውይይት እንደሚደረግባቸው ገልጸው ፤ በቢሮው በቀጣይ ሁለት ወር ሊተኮርባቸው በሚገቡ የማካካሻ ዕቅድ ዙሪያና እንዲሁም በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዋና ዋና አመላካቾች ላይም የሰላ ውይይት እንደሚደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በዚሁ መሠረት ከየሥራ ዘርፎቹ የአፈጻጸም ሪፖርት እና ዕቅድ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ኃላፊዎች እየቀረበ ይገኛል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:




Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
YouTube:
Tik Tok:





