Skip to content 
የዛሬ አንድ አሜት Resolve to Save lives የሚባል መንግስታዊ ያልሆኔ ድርጅት ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እና ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በ 8 ወረዳ እና በአንድ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ በ23 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ከተከሰቱ በብቃት ለመመከት እንዲሁም መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ሳይስተጎጉል ለማስቀጠል ዝግጁ የሆኔ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ አሃድ የመፍጠር ፕርግራም በማስጀመር ስሰራ መቆየቱ የሚታወቅ ስሆን አሁን ደግሞ የፕሮግራሙን ተደራሽነት በማስፉት በ9 ተጨማር ወረዳ 27 ጤና ጣቢያዎችን በማካተት በጥቅሉ በፕሮግራሙ የታቀፉ ወረዳዎች ቁጥር ወደ 18 ለማድረስ የታቀደ ነው።
የወርክሾፑን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል የሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሲሆን ‘Resolve to save life Ethiopia’ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር መስራት ከተጀመረ ወዲህ በመጀመሪያ ዙር በታቀፉ ተቋማት ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኖችን በጥራት መቃኘት፣በጊዜ ማሳወቅና ምላሽ የመስጠት አቅምን ከነበረበት 63% ወደ 95% ማድረስ መቻሉን በመጥቀስ የወረርሽን ቆይታ ጊዜ፥ የህመምና ሞት መጠንን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉን በሰፊው አብራርተዋል።
በወርክሾፕ ላይ በአመቱ ውስጥ በፕሮግራሙ የተመዘገቡ ምርጥ ተሞክሮዎች ለPhase 2 ለታቀፉ ወረዳዎች በስፋት የቀረቡ ስሆን በወርክሾፕ መድረክ ላይ የሲዳማ ክልል ጤና ኢንስቲትዩት ማናጅመንት አባላት ፥ የዞን ጤና ደስክ አስተባባሪዎች፥ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት እና የጤ/ጣቢያ ኃላፊዎች እንዲሁም Resolve to save life Ethiopia የPE የፕሮግራም ኃላፊዋ ወሮ ምንትዋብ ገ/እግዚአብሔር፣ የ ERPHC senior manager አቶ አሮን መብራቱ ፣ የክልሉ ERPHC program ማናጀር አቶ ተመስገን ንጉሴ ፣ የሆስፒታል መንተሮች እንዲሁም ጉዳዪ የሚመለከታቸዉ አካላት ተሳትፈዋል።
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
መጋቢት 27/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794










