Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የተቀናጀ የበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ (Integrated Disease Surveillance and Reponse at Private Health Facilities) በግል ጤና ተቋማት የማጠናከር ፕሮግራም ማስጀመሪያ ወርክሾፕ ተካሄደ።

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ በመገኝት ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስትቲዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ /Resolve to Save Lives/ለወረርሽኝ ምክንያት የሚሆኑ በሽታዎችን አስቀድሞ በመከላከል እና ዝግጁነት ላይ በ15 ወረዳዎች እና በ3 ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 50 የመንግሥት ጤና ተቋማት እያከናወነ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው ፕሮግራሙን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከመንግስት ጤና ተቋማት በተጨማሪ በተመረጡ የግል ጤና ተቋማት የተቀናጀ የበሽታዎች ቅኝት እና ሪፖርት/ምላሽ መካተቱን ገልፀው የግል ጤና ተቋማትም የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባቸው በማሳሰብ ፕሮግራሙን ውጤታማ ለማድረግ ጤና ኢንስቲትዩቱ አስፈላጊውን ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በሌላ በኩልም የፕርግራሙን አላማ ያብራሩት የሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ /Resolve to Save Lives/ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ ደሴ ፕሮግራሙ ከአለም ጤና ድርጅት በፓንዴሚክ ፈንድ በኩል በተገኘ ገንዘብ በተመረጡ በ17 መካከለኛ ክሊኒክ እና በ 5 የግል ሆስፒታሎች የሚተገበር የሙከራ ፕሮግራም መሆኑን በመግለፅ ዓላማው ከመንግስት ጤና ተቋማት ባልተናነሰ በግል ጤና ተቋማት የሚገለገል የሕብረተሰብ ቁጥር ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን የግል ተቋማትን ሳያካትቱ የሚደረግ የተቀናጀ የበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ በአንድ እጅ እንደማጨብጨብ እንደሆነ ገልጸዋል።

በመቀጠልም የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡርሶ ቡላሾ በበኩላቸው በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል ለጤናው ዘርፍ ውጤታማነት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀው ፕሮግራሙን የተሻለ ለማድረግ የመንግስት እና የግል የጤና ተቋማት ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ገልፀዉ የባለስልጣኑ መ /ቤት አስፈላጊውን ትብብርና ቁጥጥርም እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

በሲዳማ ክልል ያሉ የግል የጤና ተቋማት አሠሪዎች ማህበር ፕሬዝደንት አቶ ዮሴፍ ጌታቸው ድንገተኛ በሽታዎችን አስቀድሞ የመከላከል እና የዝግጁነት ስራ እንደ ሲዳማ ክልል ብሎም እንደ ሃገር ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር ባለመሆኑ የግል ጤና ተቋማትም ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት በጋራም እንሠራለን ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዕለቱ የጤና ተቋማት ለወረርሽኝ ምክንያት የሚሆኑ በሽታዎች ቅኝት በማጠናከር ሲከሰትም ወዲያውኑ ሪፖርት በሚደረግበት ሥርዓት ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና የተሻለ አፈጻጸም እንዲያከናውኑ የሚያስችል እና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ሰነዶች ከቀረቡ በኋላ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይትም ተደርጓል ።

በመጨረሻም የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስትቲዩት ፣ የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ፣ የሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስና /Resoleve to Save Lives Ethiopia/ የሲዳማ ክልል የግል የጤና ተቋማት አሠሪዎች ማህበር የስራ ኃላፊዎች በቀጣይ በጋራ በሚሰሩ ተግባራት ላይ የመግባቢያ ሰነድ (MOU) ተፈራርመው የግንዛቤ ማስጨበጫው መርሃ ግብር ተጠናቋል ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

መጋቢት 28/2017 ዓ.ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *