Skip to content 
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ሲሆኑ የሰባት ወር ዕቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ ኢንስቲትዩቱ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመው የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ ሰፊ የመከላከል ተግባራት የተከወኑ መሆናቸውንና ከተከሰተም በኋላ ምላሽ በመስጠት ረገድ በርካታና ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እንደተተገበሩ ገልፀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የዓለም የሴቶች ቀንን በተመለከተ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማሳለጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የሴቶችን ጥቃት ለመከላከልና ለማስቆም የወንዶችና የማህበረሰቡ ድርሻ ተተኪ የሌለው መሆኑን ገልጸው በየደረጃው ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የካቲት 29/2017 ዓ.ም
ሐዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794






