Skip to content 
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሚያዘያ 09/2017 ዓ.ም
በዕለቱ እንኳን ደህና መጥታችሁ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና እና ጤና ነክ ችግሮች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ የሕብረተሰቡ ጤና እንዲሻሻል ተቋሙ ሀላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል ፡፡
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸዉ በክልሉ የጤና ልማት ስራውን ውጤታማ በማድረግ ረገድ የምርምር ስራዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን አንስተዉ እንደ ክልል ባለፉት 3 ዓመታት ወዲህ ለውጤት እንሰራ በሚል አድስ ዘደ ተቀይሶ ትልቅ ለውጥ እንደመጣ አስታውሰው ለውጡ ዘላቂነት እንደኖረው የሁሉም ድጋፉ ያሰፈልጋል በማለት መልዕክት አሰተላልፏል።
የዕለቱ ክብር እንግዳ ና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር መሳይ ሀይሉ መልዕክት ስያስተላልፉ የሕብረተሰቡን የጤና ችግሮችን ለመለየት ጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማጠናከር የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የክልሎችን አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ከ25 በላይ የምርምር ውጤቶች መካከል 10 ተመርጠዉ ለጉባኤ የቀረቡ ስሆን ከተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተዉ በአቅራቢዎችና ከመድረክ መሪዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡
በዓዉዴ ርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ፣ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፣ የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ፣የሲዳማ ክልል ፐሬዚዳንት ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ባጥሶ ዌድሶ፣ የሲዳማ ክልል ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አየለች ሌዳሞ ፣ የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማናጅመንት አባላት እንዲሁም ከፍተኛ ኤክስፐርቶች ፣ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳርዎች ፣ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲኖችና ተመራማሪዎች፣ የጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጆች እና ለሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሚያዚያ 09/2017 ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

















