Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ሙሰኛ የሚሰርቀዉ ገንዘብን ብቻ ሳይሆን የነገ ሀገር ተረካቢዎችን መልካም አስተሳሰብ ጭምር ስለሆነ ባገኘን አጋጣሚ ሁሉ ሙሰኞችን መታገል ይገባል የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሃናጋ ።

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

መያዝያ 08/2017 ዓ. ም

ዛሬ የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና እንስትቲዩት አመራሮችእና ሰራተኞች “ሙስና ምንነት እና የመከላክያ መንገዶች” ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ::

በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉትና መድረኩን የመሩት የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሃናጋ በበኩሉ ሙሰኛ የሚሰርቀዉ ገንዘብን ብቻ ሳይሆን የነገ ሀገር ተረካቢዎችን መልካም አስተሳሰብ ጭምር ስለሆነ ባገኘን አጋጣሚ ሁሉ ሙሰኞችን መታገል እንዳለበት አስገንዝቧል ::

የሙስና ወንጀል የሚፈፀምበት መንገድ የረቀቀና በተደራጁ ሀይሎች የሚፈፀም መሆኑን ያነሱት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሃናጋ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ እንድቻል ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስቧል ። ::

በመቀጠልም በሙስና ምንነት እና የመከላክያ መንገዶች ላይ ያተኮረ የስልጠና ሰነድ በሲዳማ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የትምህርትና ስልጠና ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ወኔ ሃመሶ አማካይነት ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ተሳታፊዎችም በቀረበዉ የስልጠና ሰነድና ሪፖርት መነሻነት ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ያቀረቡ ስሆን፤ በቀረበው አስተያየትና ጥያቄ መነሻነት በአቶ ኡጋሞ ሃናጋ ፤አቶ ዮኤል ዮኦላ እና ወኔ ሃመሶ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!!

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሚያዚያ 08/2017 ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *