Skip to content 
በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት አመራርእና ሰራተኞች ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበት 7ኛ ዓመትን በዉይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
(መጋቢት 24/2017 ዓ.ም ሀዋሳ ) የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የብልጽግና ህብረት አባላትና ደጋፊዎች በኢትዮጵያ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም እውን የሆነውን ሀገራዊ ለውጥ 7ኛ ዓመትን አስመልክቶ በተለያዩ ዝግጅቶች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
‘ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!’ በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ኮንፈረንስ የተቁሙ አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ሲሆኑ መጋቢት ሀገራችን ከተጋረጠባት የመበታተን አደጋ የታደገ፤ የዘመናት የመገፋፋትና የመጠፋፋት የፖለቲካ ባህላችንን ቀይሮ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እና የበለፀገችና የተከበረች ኢትዮጵያን ለትውልድ የማሻገር ህልም የሰነቀ በታላላቅ ስኬቶች የታጀበ ሀገራዊ የለውጥ ጉዞ ዕውን የሆነበት ታሪካዊ ወር ነው ብለዋል::
አክለውም ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ በሀገራችን ታሪክ የመጋቢት ፍሬዎቻችችን ስናወሳ የመላ ኢትዮጵያዊያንን ህብረትና አንድነት ይበልጥ ያስተሳሰረና የይቻላል መንፈስን ዳግም ያጎናፀፈን የዳግማዊ አድዋ ብሔራዊ የድል ዓርማችን የሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን በጉልህ ይጠቀሳል ካለ በኃላ እነዚህ ስኬቶች ሁሉም መገንዘብ እንዳለበት ተቁመዋል ::
የበአሉ ተሳታፊዎች ለውጡ እውን ከሆነ ወዲህ የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የቀረበ ሰነድ ላይ ዉይይት እየተደረገ ይገኛል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የካቲት 24/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

